Back

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ

ሚያዝያ 11/2010

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሽግሽግና ሹመትን አጸደቀ፡፡


በዚህም መሰረት፡-

1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ …….የግብርና እና የእንስሳት ሃብት ሚንስትር
2. አቶ ሲራጅ ፈጌሳ……….የትራንስፖርት ሚንስትር
3. ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም…….የሰረተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚንስትር
4. አምባሳደር ተሾመ ቶጋ………………የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚንስትር 
5. አቶ ኡመር ሁሴን………….በሚኒስትር ማእረግ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
6. ወ/ሮ ኡባ መሀመድ ………የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚንስትር
7. ዶ/ር አምባቸው መኮንን……የኢንዱስትሪ ሚንስትር
8. አቶ ሞቱማ መቃሳ…………….የሀገር መከላከያ ሚንስትር
9. ወ/ሮ ፎዚያ አሚን…………….የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር
10. አቶ አህመድ ሺዴ…………….የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር 
11. አቶ ጃንጥራር አባይ…………………. የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር
12. አቶ መለሰ አለሙ……………..የማዕድና ኢነርጂ ሚንስትር
13. አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ……………..ጠ/አቃቤ ህግ
14. ወ/ሮ ያለም ጸጋዬ………………………..የሴቶችና ህጻናት ሚንስትር
15. አቶ መላኩ አለበል…………………..የንግድ ሚንስትር
16. ዶ/ር አሚር አማን…………የጤና ጥበቃ ሚንስትር

ጠቅላይ ሚንስትሩ የ6 ሚንስትሮችን የስልጣን ሽግሽግ፤ የ10 ሚንስትሮች አዲስ ሹመት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡

የሚንስትሮቹ የስልጣን ሽግሽግና ሹመት የተካሄደው በዋናነት የህዝብን ጥያቄና ቅሬታ እንዲሁም ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ችግር ከመፍታት አንፃር ካላቸው አቅም አኳያ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የአቅም ክፍተት ኖሯቸው እራሳቸውን ለመለወጥና ለመማር ዝግጁ የሆኑ ሚንስትሮች በካቢኔ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል ብለዋል፡፡

የህዝብን አገልግሎት ፍላጎት ለሟሟላት ዋንኛ ትኩረታቸው በመሆኑ ይህ ሊታለፍ የማይቻል መሆኑን ማወቅ እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

የመንግስትን ሃብትና ጊዜን የማባከን ሂደትን በመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ከሁሉም በላይ ግን ህዝቡን በማማረር በመንግስት ላይ የከረረ ተቃውሞዋቸውን እንዲያኑሱ የሚያደርጉትን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የመጀመሪያ ስራቸው ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡