Back

የኢትዮ-ኤርትራ ልኡካን ቡድን የአሰብ መንገድ ጥገና ሂደትን ጎበኙ

ጳጉሜ 05/2010

የኢትዮጵያና የኤርትራ የመንገድና የሎጂስቲክ  ከፍተኛ ኃላፊዎች ልኡካን ቡድን ኢትዮጵያን ከአሰብ ጋር ለማገናኘት እየተገነባ ያለውን የመንገድ ግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡

የሁለቱ ሃገራት ልኡካን ቡድንም ከሰመራ እስከ ቡሬ ድረስ ያለውን የመንገድ ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

መንገዱ ከሊሰጥ የሚችለውን ከፍተኛ ግልጋሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጥገና እና የማስፋፊያ ስራው  ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተገኝ አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንገድና የሎጂስቲክ ኃላፊዎች ከሰመራ እስከ ቡሬ ድረስ የሚገኝውን የመንገድ ሁኔታ እና የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል ፡፡

ሁለቱ ሃገራት ሰላም መፍጠራቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ የአሰብና የምጽዋ  ወደቦችን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

ይህም የሚያሳየው ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን በፍጥነት የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት ነው ብለዋል አቶ ሃብታሙ ተገኝ፡፡

 የኤርትራ ባህር ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርና  የልኡክ ቡድኑ መሪ አቶ መኮነን አበራ በበኩላቸው የመንገዱ ግንባታ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የመንገዱ ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሲጀምርም ኢትዮ- የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን፤ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማጠናከርም ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ነው የገለጹት፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ በገቡት ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ በኩል ሊስተናገዱ የሚችሉ የእቃዎችን አይነትና መጠን ግምት የመለየት ስራ እከናወነች መሆኗን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስትክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ  ናቸው፡፡

የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት