Back

ለስኳር ታማሚዎች የሚያገለግል አዲስና ቀላል የመመርመሪያ መሳሪያ ተገኘ

ታህሳስ 15/2015

ለስኳር ታማሚዎች የሚያገለግል አዲስና ቀላል የመመርመሪያ መሳሪያ ተገኘ

የስኳር ታማሚዎች በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ማወቅ የሚችሉበት አዲስና ቀላል የመመርመሪያ መሳሪያ በዘርፉ ተመራማሪዎች ተገኘ፡፡

የመመርመሪያ መሳሪያው ከወረቀት የተሰራ ሲሆን ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የሚጣል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የስኳር መጠን መመርመሪያው በምራቅ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን የሚለካ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ይህ አዲስ ግኝት ለስኳር ታማሚዎች ከዚህ በፊት ምቹ ያልሆነውን መመርመሪያ ይተካል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መመርመሪያው በዝቅተኛ ወጪ በፍጥነትና በብዛት ሊመረት እንደሚችልም ተመልክቷል፡፡

አዲሱን የስኳር መጠን መመርመሪያ ያገኙት በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ተመራማሪዎች እንደሆኑም ታውቋል፡፡  

ምንጭ፦ thehindubusinessline.com