Back

ፀሐይን እና የግብርና ተረፈ ምርትን በመጠቀም ተባዮቹን መቆጣጠር እንደሚቻል ተገለፀ

ታህሳስ 26፡ 2011 ዓ.ም

ገበሬዎች ብዙ ጊዜ እና ገንዘብን በማጥፋት አረም እና ሌሎች ተባዮችን ይቆጣጠራሉ::  አብዛኛውን ጊዜ በካይ ኬሚካሎች ውስጥ በጣም አደገኛ የሆኑ ተባዮችን በመርጨት ተባዮችን ለመቆጣጠር ይጥራሉ::

 በተጨማሪም ገበሬዎች እንደ ቆዳ ዘሮችና ቀፎዎችን  ከፍራፍሬ ምርቶች እና ከአኩሪ አተር ጋር በማቀናጀት ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን የተሻሻሉ ምርቶች  ያመርታሉ::

እነዚህ የግብርና ተረፈ ምርቶች   አደገኛ ኬሚካሎችን  በመተካት   ግብርናን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ ተመጣጣኝ እና ለአካባቢ ተስማሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚችሉ ነው የተገለፀው::

  በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ዳቪስ ውስጥ የሚገኙ ተመራማሪዎች በባዮሶላራይዜሽን ያገኘት ውጤት አመርቂ እንደሆነ ነው የገለፁት ::ይህ ምርምር የፀሐይ ሙቀትን በመጠቀም አረሞችን እና ሌሎች አፈርን የሚሸከሙ ተባዮችን መቆጣጠር እንደሚቻል ነው የገለፁት::

 የምግብ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ክሪስቶፈር ሲሞንስ  በተለያዩ ሰብሎች ላይ የባዮሶላራይዜሽን  ንጥረ-ነገርን በመሞከር ከአገር ውስጥ አርሶ አደሮች ጋር በመሥራት ላይ

እንደሚገኙ ነው የገለፁት::

 "አሁንም ገና ብዙ ስራዎች አሉን ነገር ግን ባዮሶላራይዜሽን (የተራቀቀ ለውጥ)የምርት ጥራትን   በማሻሻል ተባዮችን ለመቆጣጠር ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘላቂ መንገድ ነው"ብለዋል