Back

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ያመጡት ለውጥ የሚደነቅ ነው-ዘ ጋርዲያን

ታህሳስ 30፤ 2011 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡

ይሁንና ለውጡ ዘላቂ ለማድረግ ተቋማትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብሏል በርዕሰ አንቀጹ ባሰፈረው ጽሁፍ፡፡

በአገሪቱ ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች መተካቱ በሀገሪቱ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል፡፡

አልፎ አልፎ እዚህም እዚያም የሚከሰቱ አንዳንድ ችግሮችን መፍታት እንዲያስችል ለውጡ ተቋማዊ እንዲሆን አጥብቆ መስራት ያስፈልጋል ይላል ዘ ጋርዲያን ያስነበበው ጽሁፍ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአገር ውስጥና በአካባቢው አገራት በርካታ የሚያቀራርቡ ስራዎችን መስራታቸው በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ምንጭ፡- ዘጋርዲያን