Back

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ‘‘ሃያት" ሆቴል በአዲስ አበባ ተከፈተ

ታህሳስ 30፣ 2011 ዓ.ም

በአለምአቀፍ ደረጃ የሚታወቀው ‘ሀያት ሆቴል’ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አከባቢ ለስራ ክፍት ሆኗል፡፡

ሆቴሉ 188 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 12 ቅንጡ ክፍሎችና ሌሎች ለባለስልጣናትና በተለያዩ ደረጃ ላሉ ሰዎች የተዘጋጁ ናቻው፡፡

የሆቴሉ ዋና ሀላፊ ‘ሄዶ ሲብስ’ በመክፈቻ ስነ–ስረዓት ላይ በአዲስ አበባ ሃያት ሆቴልን በመክፈታቻው የተሰማቻውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በሌሎች አገራት የሚያውቁን ደንበኞቻችንና፣የአለምአቀፍ መንገደኞች በአዲስ አበባ በከፈትነው ሀያት ሆቴል እንደሚደሰቱ ሙሉ እምነት አለኝም ብለዋል፡፡

በሆቴሉ ሬስቶራንቶች፣ባሮች፣ላውንጅና፣የስፖርት ማጎልበቻ ማዕከሎችም ይገኙበታል፡፡

1700 ስኩዌር ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽም አለው

ምንጭ፡ራስ ቱርዝም ኒውስ