Back

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንችስተር በረራ የማድረግ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

ታህሳስ 30፣ 2011 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር  መንገድ  ወደ እንግሊዝ  ማንችስተር ከተማ ከለንደን ቀጥሎ ሁለተኛ የረራ መደረሻዉን የመጀመር  ዕቅዱን ይፋ አደረገ

አየር መንገዱ በቦይንግ B787 ወደ ማችስተር ከተማ በረራ የመጀመር ዕቅዱን ይፋ ባደረገበት  ስነ ስራዓት ላይ የእንግሊዝ አምባሳደር ሱዛና ሙርሄድና የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጸሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተገኝተዉ ነበር

በሳምንት 4 ቀን ወደ ማንችስተር በረራ የሚደረግበት ይህ የማስጀመሪያዉ  ስነስራዓት ደማቅና ያማረ እንደነበር ሚስተር ሱዛን ተናግረዋል

የኢትዮጲያ አየር መንገድን ሳስብ ኢትዮጲያን አያለሁ ያሉት ሙርሄድ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዓለም ዓቀፍና በማደግ ላይ ያለ፤ ዘመናዊና ሰዎችን ከሰዎች ጋር የሚያገኝ፤በዕድገቱ ወደፊት እየገሰገሰ ያለ፤በዓይነቱ ልዩ የሆነ አየር መንገድ መሆኑንም ሚስተር ሱዛን ተናግረዋል

አየር መንገዱ ወደ እንግሊዝ ማንችስትር በረራ መጀመሩ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ምን ያህል ጠንካራና ጥልቅ እንደሆነ ያመለክታል ያሉት ሚስተር ሱዛን ይህ ተግባር እሳቸዉ አምባሳደር በሆኑበት ወቅት በመፈጸሙ ዕድለኛ ነኝ ብለዋል

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በበኩላቸዉ አየር መንገዱ ወደ እንግሊዝ ለመብረር አዲስ አይደለም ከ46 ዓመት በፊት ወደ ለንደን የኢትዮጲያ አየር መንገድ በረራ ስያደርግ ነበር ብለዋል፡፡ በማስጀመሪያ ስነስራዓቱ ላይ በመገኘታቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉንም ገልጸዋል

እናም አሁን ወደ ማንችስተር የአየር መንገዱ ተጠቃሚ ደንበኞች  ወደ አሉባቸዉ አካበቢዎች የበረራ መደራሻ ለመክፈት በመወሰናችን ደስተኛ መሆናቸዉን ገልጸዋል

አየር መንገዱ ከአፍርካ ወደ አወሮፓ የሚያርገዉ በረራ ንግድና እንቨስትመንትን በማጠናከር፤ የቱሪዝምና የህዝብ ለህዝብ ግንኝነትን በማጠናከር የሚጫወተዉ ሚና ቀላል አይደለም  ብለዋል ዋና ስራ አስፈጸሚዉ