Back

በሙስና የተጠረጠሩት የቀድሞ የሞዛምቢክ የፋይናንስ ሚኒስትር ክስ ተመሰረተባቸው

ጥር 01/ 2011

በሙስና የተጠረጠሩት የቀድሞ የሞዛምቢክ የፋይናንስ ሚኒስትር ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞው የሞዛምቢክ የፋይናንስ ሚኒስትር ኢማኑዌል ቻንግን ጨምሮ 17 ግለሰቦች በ2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሙስና ቅሌት ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ክሱ የተመሰረተባቸው በአገሪቱ የዓሳ ስጋ ማቀነባበሪያ የሆነውን ኩባንያ አቅም ለማሳደግ ከ2 ባንኮች ብድር በመጠየቅ ሂደት በተፈጸመ ሙስና እንደሆነ ነው የአገሪቱ ዓቃቤ ህግ የገለጸው፡፡

ዓቃቤ ህግ በክሱ እንዳመለከተው በሙስና ወንጀሉ የተከሰሱት የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች ተሳታፊ ዜጎች፤ ስልጣንን አላግባብ ተጠቅመው የህዝብን እምነት ያሳጡ አካላት፤ አጭበርባሪዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ በማተም ተግባር የተሳተፉ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል፡፡

በግለሰቦቹ ላይ ክሱ የተመሰረተው በ2013 በሞዛምቢክ የዓሳ ስጋ ማቀነባበሪያ ኩባንያ ለማልማት በሚል የብድር ድርድር በተደረገበት ወቅት የገንዘብ ማጭበርበር ተግባር ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ 3 የስዊስ ባንክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ከቀናት በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ከ18ቱ ተከሳሾች አንዱ የሆኑት የ63 ዓመቱ ኢማኑዌል ቻንግ በጎረቤት አገር ደቡብ አፍሪካ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ወንጀሉን መፈጸማቸውን በማስተባበል ላይ ናቸዉ፡፡

ደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ሞዛምቢክ በ2016 የብድር መጠኗን ባለማሳወቁዋ ምክንያት ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋምና የተራድኦ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ማቆማቸውን በመግለጸቸው አገሪቱ የውጭ ምዛሪ እጥረት ውስጥ መግባቱዋ፤ የውጭ ብድር ጫናው መጨመሩ እንዲሁም የብድር ወለድ የመቋቋም አቅም ማጣቷ እየተነገረ ነው፡፡

ምንጭ፡- africanews.com