Back

ኪም ጆንግ ኡን ከ3 ቀን የቻይና ጉብኝት በኋላ ወደ አገራቸው ተመለሱ

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ድንገተኛ የቻይና ጉብኝት  በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱ ሲሆን፣ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ለሁለተኛ ጊዜ መገናኘት የሚለውንም ሀሳብ ደግፈዋል፡፡  

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት  ከስድስት ወራት በፊት ተገናኝተው የነበረ ሲሆን፣ የኒውክለር ውይይታቸው ግን ከዚያ ወዲህ እምብዛም ለውጥ አላሰየም፡፡

የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ሁለቱ መሪዎች በድጋሜ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ቻይና ሁለቱ አገራት የሚያደርጉትን ውይይት እንደምትደግፍና ሁለቱ አገራት ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንደሚፈቱም ያላትን ምኞች ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ:-  ቢቢሲ