Back

አማራ ክልል የግብር አሰባሰቡን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ ይፋ አደረገ

ጥር 26፣2011

አማራ ክልል የግብር አሰባሰቡን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ ይፋ አደረገ፡፡

‹‹ግዴታየን እወጣለሁ መብቴንም እጠይቃለሁ›› በሚል መሪ  ይፋየደረገውን የግብር ንቅናቄ ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው፡፡

በክልሉ የሚሰበሰበውን ግብር ለማሳግ ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ እና አመራሩና ባለድርሻ አካላት ደግሞ ቅንነት የተሞላበት አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ መንግስት በሚሰበስበው ግብር የህበረተሰቡን ሰላም ፣ደህንነት ይጠብቃል፡፡ የልማት ጥያቄውንም እንደሚመልስ መናገራውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የግብር ንቅናቄ ይፋ ከተደረገ በኋላ ክልሎች በራሳቸው መንገድ የታክስ አሰባሰቡን ለማሳደግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡