Back

በለንደን የመጀመሪያው የምድር ውስጥ እርሻ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ

ጥር 28/ 2011

በዓለም የመጀመሪያ የሆነው የምድር ውስጥ እርሻ በእንግሊዝ አገር ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑን ሎንሊፕላኔት ዘገበ፡፡

ይህ የምድር ውስጥ የአትክልት ምርትን በቁመት የሚመረትበት እርሻ የተለየና ጎብኚዎችን የሚያስገርም ስፍራ እንደሆነ ነው የተዘገበው፡፡

ይህ 33 ሜትር የምድር ውስጥ የሚገኘው ስፍራ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ምሽግ የነበረ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ይህ ተግባር ሀይድሮፖኒክ ዘዴን  እና ኤልኢዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በምድር ውስጥ አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎችንና ሰላጣን ማምረት እንደሚቻል ያሳየ ግኝት ነው፡፡

በዚህም፣ በግብርናው ዘርፍ ከተባይና ከአየር መለዋወጥ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ውጣውረድ ማላቀቅ የቻለ ዘመናዊ የእርሻ ስራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህ የሽቅብ ወይም የቁመት ግብርና በፕሪስተን ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ምሁራን ሪቻርድ ባርድ እና ስቴቨን ድሪንግ እኤአ በ2014 ያስተዋወቁት መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

ምንጭ፡- ሎንሊ ፕላኔት