Back

የአፍሪካን የጤና ጥበቃ ጉዳዩችን ለማሻሻል መሪዎቿ አዲስ አበባ ላይ ይመክራሉ

ጥር 30፡ 2011 ዓ.ም

የአፍሪካ ሃገራት ለጤና ጥበቃ የሚመድቡት በጀት ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱ የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ተቋሙ የ2018 የሃገራት ለጤና የሚያወጡትን ወጪ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳመለከተው ከ55 የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት 35ቱ በተጠናቀቀው የፈረንጆች ዓመት ለጤና የሚመድቡት በጀት ጭማሬ አሳይቷል፡፡

ሃገራቱ ለጤናው የሚበጅቱትን በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ ቢጨምርም በሚልዮን የሚቆጠሩ አፍሪካዊያን አሁንም በየዓመቱ መከላከል ከሚቻል በሽታዎች ህይወታቸው እያለፈ ነው፡፡

ይህን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ ጋር ተያይዞ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ምክክሩ መንግሥታት ከግል ባለሃብት እና ዓለም አቀፍ የልማት ማሕበረሰብ ጋር በማገናኘት ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋንን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፤ አይቲ አፍሪካ