Back

የጊኒው ፕሬዝደንት አልፋ ኮንዴ ኢስተርን ኢንዱስትሪያል ዞንንን ጎበኙ

የካቲት 1፡ 2011

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢስተርን ኢንዱስትሪያል ዞንንን ከጊኒው ፕሬዝደንት አልፋ ኮንዴ ጋር ጎበኙ፡፡

 

በጉብኝቱ ወቅት የኢንቨስተመንት ኮሚሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርኩ ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

በገለፃው መሰረት ከ15 ሽህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፤ በቀጣይ ይህንን እጥፍ ለማድረግ የማስፋፊያ ስራ እንደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡

 

ከጊኒው ፕሬዝደንት ጋር የመጡ የልዑካን ቡድኑ አባላት ከኢንዱስትሪ ፓርኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ትልቅ ትምህርት እንደቀሰሙ ተናግረዋል፡፡


ፎቶ፡- ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት