Back

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የናይጀሪያን ምርጫ ታዛቢ ቡድን ይመራሉ

የካቲት 2፡ 2011 ዓ.ም
የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ህብረት የናይጄሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚመሩ በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽነር አስታወቁ።

ኮሚሽነሯ ሚናታ ሳማታ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ በቅርቡ ወደ ናይጄሪያ በማቅናት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለመላክ ከስምምነት ደርሰዋል።

የናይጄሪያ ምርጫ የካቲት 9 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡