Back

የብሪታንያ ብዝሃ ህይወትን በመጠቀም ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን በማስወገድ በዓለም የመጀመሪያ ሆነች

የካቲት 2፡ 2011 ዓ.ም

የብሪታንያው ድራክስ ብዝሃ ህይወትን በመጠቀም ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአካባቢው በመምጠጥ በዓለም የመጀመሪያ ሆነ

ድራክስ የተሰኘው የብሪታንያ ኩባንያ በሰሜን ዮርክሻየር የሚገኘው እጨትን በመጠቀም  ሃይል በሚያመነጭበት ቦታ ካርበን ዳይ ኦክሳይድን ከከባቢ አየር መምጠጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረግ በዓለም የመጀመሪያ ሆኗል፡፡

ሃየል አምራች ጉባንያዎች ይሄን ቴክሎኖጂ በመጠቀም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ብክለትን በመቀነስ ቀጣይ የሆነ የሃይል አቅርቦት ማቅረብ እንደሚያችላቸው ተገልጿል፡፡

ቴክሎኖጂው በቀን አንድ ቶን የካርቦን ዳይ ኦክሳይድን መምጠጥ የሚችል ሲሆን ይህም ቴክሎኖጂው ከተስፋፋ በካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የሚከሰተውን ብክለት ይቀንሰዋል ተብሏል፡፡

የብሪታንያው የሃይል እና ጽዱ እድገት ሚኒስቴር ሚኒስትር እንደተናገሩት የፈጠራ ቴክሎኖጂው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር እና ከካርቦን ዳይ ኦክሳድ ነፃ የሆነ ኢንዱስትሪዎች በብሪታንያ እንዲኖሩ ያግዛል ብለዋል፡፡