Back

የግብር ፍትሃዊነት ትብብር ፕሮጀክት ጽ/ቤት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ

የካቲት 13/ 2011

የአገራዊ የታክስ ንቅናቄው አንድ አካል የሆነዉ የግብር ፍትሃዊነት ትብብር ፕሮጀክት ጽ/ቤት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በስነስርአቱ ላይ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በገቢዎች ሚኒኒስቴር ስልጠና ተሰጥቷቸዉ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ታቅፈዉ የማህበረሰቡን የግብር ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተጠቁሟል፡፡

የግብር ፍትሃዊነት ትብብር ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በአዲስ አበባ መርካቶ፣ ሾላ ገበያ እና ኮልፌ ላይ በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ፡፡

በቀጣይም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ አዳማ፣ አዋሳ እና ሌሎች ከተሞች ላይ ስራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

በንግዱ ውስጥ ሆነው ገቢ እያገኙ ግብር የማይከፍሉ የንግድ ማህበረሰብ በመኖራቸው እየተሰበሰበ ያለዉ ግብር ዝቅተኛ መሆኑ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልፆአል፡፡

ሪፖርተር፡- ተመስገን ንብረት