Back

በሀዋሳ የሲዳማ ብሄረሰብ በክልል መደረጀትን አስመልክቶ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ

የካቲት 14፡ 2011 ዓ.ም
በሀዋሳ የሲዳማ ብሄረሰብ በክልል መደረጀትን አስመልክቶ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡

በሰልፉ "ህገ መንግስቱ ይከበር"፤ "ሪፎርሙን እንደግፋለን" ፤"ሪፈረንደሙ ይፍጠን"ና መሰል መልዕክቶችን የያዙ ጽሁፎች ተላልፈዋል፡፡

ሰልፉ የሲዳማን በክልል የመደረጀት ጥያቄን ያነገበ ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ቃሬቻ ዊጫና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ካንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ በክልል የመደረጀቱ ጥያቄዉ 130 ዓመታት ያህል የቆየ ጥያቄ መሆኑን አቅርበዋል፡፡

ደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔዉን በአርባ ምንጭ እያካሄደ በመሆኑም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሰልፉ አለመገኘታቸው ተገልጿል ፡፡

በኬኔዲ አባተ