Back

የጎግል ኩባንያ የካናዳ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የፖለቲካ ማስታወቂያ እንዳይለቀቅ ከለከለ

የካቲት 26፡ 2011 ዓ.ም

ካናዳ በሀገሪቱ ባወጣችው ጥብቅ የማስታወቂያ ደንብ መመሪያ ምክንያት የጎግል ኩባንያ ማንኛውም ማስታወቂያ ከካናዳ ምርጫ በፊት እንዳይካሄድ አግዷል::

እ.ኤ.አ በ2019 ታህሳስ ወር በተደነገገው ቢ-76 ህግ መሰረት ማንኛውም የፖለቲካ ማስታወቂያ ከምርጫው በፊት በካናዳ እንዳይተላለፍ በተባለው መሰረት የጎግል ኩባንያ መከልከሉን ገለጿል::

በካናዳ የሚገኝው የጎግል ኩባንያ ወኪል እንዳስታወቀው በካናዳ ለሚካሄድው ምርጫ ከፖለቲካ ማስታወቂያ ውጪ የሆነ ህብረተሰቡን ወቅታዊ መረጃ በማሰተላለፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል::

ምርጫው የሚካሄደው እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር መሆኑም ታውቋል::

እንዲህ ዓይነቱ ማስታወቂያ በጎግል ኩባንያ ሲከለከል ይህ ለጀመሪያ እንደሆነ ተገልፅዋል።

ምንጭ ሮይተርስ