Back

በሴኔጋል ምርጫ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል አሸናፊ ሆኑ

የካቲት 27/ 2011

የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እኤአ የካቲት 24 በተካሄደው ምርጫ 58 ከመቶ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

የሴኔጋል ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱ ዳግም አገሪቷን ለመምራት የሚያስችላቸውን አስተማማኝ ድምፅ በማግኘት ማሸናፋቸውን ነው ይፋ ያደረገው፡፡ 

ፕሬዚዳንት ሳል በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው የምዕራብ አፍሪካይቱን ሃገር ከአህጉሪቱ ከፍተኛው ደረጃ ላይ የተቀመጠውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከ6 በመቶ በላይ   እንድታስመዘግብ በማድረጋቸው እንደሚያሸንፉ የቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸው እንደነበር ነው የተገለፀው። 

"እንደገና  በኔ ላይ  እምነት  መጣላችሁ  የበለጠ እና የተሻለ ለማድረግ እንድሰራ ያነሳሳኛል" ብለዋል  ፕሬዚዳንቱ  ለሪፖርተሮች።

ምክር ቤቱ ኢድሪሳ ሴክ 21 በመቶ ኡስማኔ ሶንኮ 16 በመቶ ድምፅ በማግኘት 2ኛና 3ኛ እንደወጡ አረጋግጧል።      

ለምርጫው ከተመዘገቡት 6.7 ሚሊዮን በላይ መራጮቸ ከ66 በመቶ በላይ ተገኝተዋል ነው የተባለው።

ምንጭ፡- ሮይተርስ