Back

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተስማሙ

መጋቢት 3/ 2011

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በመከላከያ፣ በኢንቨስትመንት እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሚንስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ከፈረንሳይ አቻቸው ፍሎረንስ ፓርሊ ጋር በመከላከያ በአቅም ግንባታ፣ በስልጠና እንዲሁም እስትራቴጃዊ ልምድ ልውውጥ አብሮ ለመስራት ስምምነት ፈርመዋል፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የፋይናንስ ትብብር እንዲሁም የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዥዋን ኢብስ ሌድሪያን ተፈራርመዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በብሄራዊ ቤተመንግስት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የእራት ግብዣ ይደረግላቸዋል፡፡

ከሁለት ቀን የኢትዮጵያ ጉብኝት በኋላ ወደ ኬንያ በመጓዝ በናይሮቢ የሚካሄደውን የአንድ ፕላኔት የመሪዎች ጉባኤ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በጋራ እንደሚመሩ ይጠበቃል።

በአበበ ሞላ