Back

አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ችግር የራሷን መፍትሄዎች ትፈልጋለች

መጋቢት  6/ 2011

መሪዎችና ባለሙያዎች አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቀነስ የራሷን መፍትሔ ማግኘት እንዳለባት አሳሰቡ።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማንዌል ማክሮን እንደገለጹት በዘመናዊው  ዓለም  እንደ ድንጋይ ከሰልና ነዳጅ  ያሉ የኃይል ምንጮች  የአየር ብክለትን ስለሚያስከትሉ  ከዚሀ በኋላ እነሱን ለኢንዱስትሪ መጠቀም አስፈላጊ አይደለም ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት የአከባቢ ጥበቃ አንድ ፕላኔት በሚል ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ 

የአረንጓዴውን ሃይል ወደፊት በማስቀጠል 75 ከመቶ  የተፈጥሮ ሀብቷን ከአረንጓዴ ሃይል የምታገኘውን የኬንያ ምሣሌ  አለማችን እንድትከተል ፕሬዝዳንት  ማክሮን  ጥሪ አቅርበዋል።

የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ የመጀመሪያዎቹ ተፅዕኖዎች በአህጉሪቱ ስለሚታዩ ለዚህ ትግል ዋነኛው መንስኤ እንደሆነ ነው ማክሮን የገለፁት።

ምንጭ  ፎክስ ኒውስ