Back

በጃፓን አባቶች ልጆቻቸውን ማጥባት የሚያስችል መሳሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

መጋቢት 16/ 2011

አንዳንድ ግዜ አባቶች ከእናቶች ጋር የሚለያያቸው ነገር ቢኖር ልጅ መውለድና ማጥባት ብቻ እንደሆነ ይከራከራሉ ።

ምስጋና ይግባው እና በጃፓን ዴንቱሱ በተባለ ኩባንያ አንድ መሳሪያ ሰርቶ አባቶች መውለድ እንኳ ባይችሉ ማጥባት እንዲችሉ በማድረግ አባቶች እንዳይቸገሩ ሊያደርግ ነው።

አንዳንድ ዳታዎች እንደሚያሳዩት አባቶች ልጆችን የመመገብ እና የማስተኛት ብቻ የነበረው ሃላፊነት በመጨመር ማጥባት እንዲጀምሩ አድርጓል በዚህም የእናቶችን ሃላፊነት መቀነስ እንዲያስችልው ተገልጿል።

የማጥቢያ መሳሪያው የተሰራው የእናቶችን ተፈጥሯዊ ይዘቱን በመጠበቅ ልክ እንደ እናቶች ጡት መቀት ያለው ፣ የጡት መሳሪያው በመርገብገብ የሚጠባው ህጻን እንዲተኛ የሚያደገው መሆኑ ደግሞ መሳሪያውን ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል።

የማጥቢያው መሳሪያ አሁንም ቢሆን ተግባራዊ ባይሆንም አንድ ቀን አባቶች ማጥባት የሚጀምሩበት ግዜ ግን ሩቅ እንደማይሆን ታውቋል።

ምንጭ፣ ኦዲቲ ሴንትራል