Back

በቅርቡ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከበረራ በፊት ደህንነትቱ የተጠበቀና አነሳሱም ቢሆን ትክክለኛውን አቅጣጫ የተከተለ እንደነበር የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቡድኑ አስታወቀ፡፡

መጋቢት 26፣2011

በቅርቡ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከበረራ በፊት ደህንነትቱ የተጠበቀና አነሳሱም ቢሆን ትክክለኛውን አቅጣጫ የተከተለ እንደነበር የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቡድኑ አስታወቀ፡፡ 

መጋቢት 1 ፣2011 ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ እያለ ስለተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕን የአደጋ ምክንያት ቅድመ ሪፖርት ይፋ ሆኗል፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር ያለው የአውሮፕላን አደጋ የምርመራ ቡድን ከአውሮፕላን አምራቹ ኩባንያ፣ከአሜሪካ ፣ ከፈረንሳይና አውሮፓ ህብረት የተውጣጡ የአቬሽን ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሩሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የቅድመ ምርመራውን ግኝት ይፋ አድርገዋል፡ ፡

በዚህም መሰረት አውሮፕላኑ መብረር በሚያስችል አቋም ላይ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

አውሮፕላኑ ሲነሳም በመብረር በሚችልበት አቅጣጫ ላይ እንደነበርና አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን መመሪያ ተከትለው ለመቆጣጠር ጥረት አድርገው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ አደጋው መከሰቱን ሚንስትሯ አመልክተዋል፡፡

የምርመራ ሂደቱ አለም አቀፍ ህጎችን ተከትሎ የተጀመረ ሂደት መሆኑን ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታውቀዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ የምርመራ ውጤቱ ተጠናቆ እንደሚገለፅ የአውሮፕላን ምርመራ ቡድኑ አስታውቋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ አደጋውን መነሻ በማድረግ በቀጣይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮችም ምክረ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በበረራ ወቅት ለመቆጣጠር እንዲያስችል የተገጠመለት ስርዓት አምራቹ ኩባንያ በድጋሜ ሊፈትሸው እንደሚገባ አመልክቷል፡፡

አገራትም አውሮፕላኑ ወደ ስራ ከመመለሱ በፊት በበረራ ወቅት የሚያጋጥመውን የመቆጣጠር ችግር በአግባቡ መቆጣጠር መቻሉን ቢያረጋግጡ የሚል ምክረ ሀሳብም ቀርቧል፡፡

በእዮብ ሞገስ