Back

ቻይናውያን ሰላም አስከባሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው

መጋቢት 26፣ 2011 ዓ.ም

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊባኖስ ጊዚያዊ የፀጥታ ሃይል ስር ተልዕኳቸውን በመፈፀም ላይ የሚገኙ ቻይናውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለአበረከቱት አስተዋፅኦ የመንግስታቱ ድርጅት የሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተላቸው ፡፡

ዝግጅቱ የተካሄደው በደቡባዊ ሊባኖስ ሃኒያህ በተባለ ቦታ በቻይናውያን ወታደሮች ካምፕ ሲሆን በዝግጅቱም የተልዕኮው አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ስቴፋኖ ደልኮል ፣በሊባኖስ የቻይና አምባሳደር ዋንግ ከጅያን እና የሊባኖስ ወታደራዊ ሃይል ተወካይ ተገኝተዋል፡፡

በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ሜጀር ጀኔራል ሽቴፋኖ ደልኮል ባደረጉት ንግግር “የተሰጣችሁ የሜዳሊያ ሽልማት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊባኖስ ጊዜዊ ሰላም ማስከበር ለበረከታችሁት አስተዋፅኦ ምስጋና እና በህይዎት ዘመናችሁ ወርቃማ ማስታዎሻ እንዲሆናችሁ ነው” ብለዋል፡፡

"በፀጥታው ምክር ቤት የህግ መዕቀፍ ስር ለፈፀማችሁት ጀብድ፣ ለነበራችሁ ዝግጁነትና ቁርጠኝነት እንዲሁም ለፈፀማችሁት ሞያዊ ተግባር ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉም” ጀኔራሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

በለፉት 11 ወራት በሊባኖስ የሚገኘው የቻይና ሰላም አስከባሪ ሃይል ከ 6 ሽህ 690 ስኩሄር ሜትር በላይ በፈንጅ የታጠሩ ቦታዎችን በማፅድት፣ከ 1 ሺህ 400 በላይ የተቀበረ ፈንጅ ማምከንን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፡-ቻይና ዴይሊ