Back

በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ያሰጋኛል - ደቡብ ሱዳን

ሚያዚያ 04፣ 2011

በሱን በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት አገሪቱን ለሶስት አስርት ዓመታት የመሯት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መወገድ የጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት እንዳያደናቅፈው አዲሲቱ አገር ሰግታለች፡፡

በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር እና የቀድሞ ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል ለተፈረመው የሰላም ስምምነትና የጥምር መንግሥት ምስረታ ሱዳን ቁልፍ ሚና መጫወቷ አይዘነጋም፡፡

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኢሊያ ሎሞሮ እንደገለጹት ሱዳን በደቡብ ሱዳን ሰላም እና መረጋጋት አንዲመጣ በጣም ጥራለች፤ በመሆኑም የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ስልጣን ላይ መቆየት ለደቡብ ሱዳን ዋትና ነበር ብለዋል፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ