Back

በኢትዮጵያ የታየው የሚዲያ ነፃነት የአገሪቱን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ የመጣ ነው፡- ፕ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ሚያዝያ 24፣2011

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው ፖለቲካዊ ማሻሻያ ለሚዲያው ነፃነት የተሻለ በር መክፈቱን ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለፁ፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ባለው በአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ላይ ተገኝተው እንዳሉት አገሪቱ በአለም የፕሬስ ነፃነት ደረጃዋን ማሻሻል የቻለችው እየተወሰደ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ የአለምን መገናኛ ብዙሃንን ሚና በተለየ አቅጣጫ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል ያሉት ፕሬዝዳንቷ፣ በተለይ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃዎች ለኢትዮጵያም ፈተናዎች ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ተፅዕኖ የንግግር ነፃነትን ሳይገድብ በንቁ የዜጎች ተሳትፎ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

የአለም ፕሬስ ቀን ተሳታፊዎችም በተመሳሳይ መልክ ማህበራዊ ሚዲያው እየጋረጠ ያለውን አሉታዊ ስጋት ለማስወገድ የመፍትሄ ሀሳብ ያመነጫሉ ብለው አንደሚያምኑም ተናግረዋል፡፡

ዩኒስኮም ዓመታዊ የሰላም ሽልማቱን ለኢትዮጵያው መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መስጠቱ በኢትዮጵያ መንግስት ስም ፕሬዝዳንቷ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡