Back

የዓለም ሙቀት መጠን በ2 ድግሪ ሊጨምር እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ

ሰዎች የነዳጅ ዓይነቶችን መጠቀማቸው፤ ደኖች በመመንጠራቸዉ የከባቢ አየር ብክለት መጠን እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡

ምድር ተፈጥሮዓዊ የቅዝቃዜ ኡደቷን ጠብቃ እንዳትቆይ አድርጎታል ፡፡ በመሆኑም  የዓለም የሙቀት መጠን  አስፈሪ በሆነ ሁኔታ በተከታተይ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡

በዓለም መንግስታት የሚወስዷቸው የመፍትሄ እርምጀዎች ካልፈጠኑ በስተቀር የዓለም የሙቀት መጠን በአማካይ በ1 ድግሪ ሴልሽየስ መጨመሩ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡

ሰባ ባለሙያዎች የተሳተፉበት አንድ ጥናት እንደመለከተዉ የዓለም ሙቀት መጠን በ2 ድግሪ የሚጨምር ሲሆን ለሰዉ ልጅ ጤና እጅግ አስግ የሆኑ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡

በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ህዝቦች 37 በመቶ የሚሆኑት በየ5 ዓመት ልዩነት ለሙቀት ወጀብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ፤3 መቶ ሰማኒያ ስምንት ሚሊየን ህዝቦች ለዉሃ እጦት  እንደሚጋለጡ፤ 1መቶ 94 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ለከፋ ድርቅ ሊጋለጡ እንደሚችሉም እየተነገረ ነዉ፡፡

ጎርፍና ከባድ ዉሽንፍር የቀላቀለ ዝናብ መብዛት፤ ሰደድ እሳት፤ የደኖች ቃጠሎና ምርታማነት መቀነስ፤ 1 ሚሊየን የሚጠጉ ብዘኃ ህይወት ከምድረ ገጽ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸዉ መሆኑ፤ የዓለማችንን 27 በመቶ የወባ ትንኝ ወረርሽኝ ሊያጠቃት እንደሚችል በጥናቱ ተመለክቷል፡፡

ችግሩ ለዓዘመናት ስነገር የቆዩ ቢሆንም አሁን ግን አፋጣኝ መፍትሄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን ብለዋል ጥናት አቅራቢዎቹ፡፡

ዛፎችን አለመቁረጥ ፤ ችግኝ መትከልና  ካርቦንን ከከባቢ አየር መሳብ የሚችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በፈጠራ መልክ ወደ መጠቀም መግባት አስፈላጊ ነዉ ያለዉ ጥናቱ ለተግባርነቱም  ፈጣንና አሪቆ በመሳብ ላይ የተመሰረተ በህብረተሰቡ ዉስጥ ለዉጦችን ማምጣት የሚችሉ ሁኔታዎችን ፈጥሮ መስራት አስፈላጊ ነዉ ብለዋል፡፡