Back

አንድ የናይጄሪያ ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪና መስራቱ ተነገረ

ሐምሌ 2 ቀን 2011 ዓ.ም

በንሱካ ከተማ የሚገኘው የናይጄሪያ ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪና መስራቱ ተነገረ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተሰራችውና ‘ላየን ኦዙምባ 551’ ተብላ የተሰየመችው መኪና ባለ 5 መቀመጫ እንደሆነች ነው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የገለጹት፡፡

የናይጄሪያ ብሔራዊ አውቶሞቲቭ ዲዛይንና ማምረቻ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ጄላኒ አሊዩ በአገሪቱ የሚገኙ ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዩኒቨርሲቲውን አርአያነት በመከተል ለቴክኖሎጂ ፈጠራ  ተገቢውን ትኩረት  እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡- vanguardngr.com