Back

የአፍሪካ ህብረት የሽብርተኝነት ድርጊቶችን ለመከላከል የበይነ መረብ እንቅስቃሴ ላይ ክትትል እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት የሽብርተኝነት ድርጊቶችን ለመከላከል የበይነ መረብ እንቅስቃሴ ክትትል እንዲደረግበት ጥሪ አቅርቧል።

የአፍሪካ ኅብረት የሽብር ምርምር እና ጥናት ተቋም ምክትል ዳይሬክተር ኢድሪስ ሙኒር ላላሊ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ሽብርተኞች የሽብርተኝነት በይነ መረቦችን ተጠቅመው የወንጀል ተግባራቸውን ለመፈፀም ዕቅድ አውጥተዋል ብለዋል።

ሙኒር ኢድሪስ ላላሊ በአፍሪካ አህጉራዊ የውይይት መድረክ ላይ የአፍሪካ ሽብርተኝነት እና የአክራሪነት ንቅናቄን ለመከላከል የአህጉሪቱን ደህንነት በማሻሻል የሽብር ተግባሮችን መከታተል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ሌሎች አህጉራት የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ተከታትለው የሽብር ተግባራትን በማክሸፍ ረገድ ውጤታማ ሆነው መገኘታቸውን የጠቀሱት ላላሊ የአፍሪካ መከላከያ ኤጀንሲዎችም በዲጂታል የመሳሪያ ስርዓቶች ላይ ያላቸውን ቁጥጥር አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

"ፈተናው ከአፍሪካ ውጪ የሚሰሩ አብዛኛዎቹ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች በአፍሪካ አህጉር ላይ የሽብር ወንጀለኞችን ለመክሰስ በበይነ መረብ ላይ የሚገኝን መረጃ እንዲሰበስቡ ማድረጉ ነው" ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሳይበር ደህንነት እና የግል መረጃዎች ጥበቃ ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ. በ2014 ፀድቋል። ላላሊ እንደገለጹት በርካታ የአፍሪካ አገራትም ከዚህ በመነሳት የየራሳቸውን ፕሮቶኮል አዘጋጅተዋል።

ስምምነቱ አባል መንግስታት በበይነ መረብ በሚፈጸም ወንጀል ላይ ልዩ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ ያቀርባል ነው ያሉት ኢድሪስ ሙኒር ላላሊ።

ምንጭ᎓- ዥንዋ