Back

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንድ እና ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 03፡ 2011 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ አቪስቶ እና ከኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ካንግ ኩያንግ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም በኢትዮጵያና በፊንላንድ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የተላከ መልዕክትም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አድርሰዋል፡፡

ፊላንድ የወቅቱ የአውሮፓ ህብረት ሊቀመንበር እንደመሆኗ በውይይታቸው ከሀገራቱ ግንኙነት ባለፈ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ በሚያደርጋቸው ድጋፎች ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀቪስቶን ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ የጀመሩትየደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ዋነኛ አጋር ናት ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ካንግ ኪዮንግዋ ይህንንም የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተጀመረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን ሀገራቸው እንደምታደንቅ የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በትምህርትና ስልጠና ኢትዮጵያን ለማገዝ መስማማቷን የገለፁት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደቡብ ኮሪያን እንዲጎበኙ መጋበዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር፡- አስማማው አየነው