Back

ኢትዮጵያና አየርላንድ ለፓርላማ ማሻሻያ አጀንዳ የሚውል የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ከሆኑት ሶንያ ሃይላንድ ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ አየርላንድ ለኢትዮጵያ የፓርላማ ማሻሻያ አጀንዳ ድጋፍ በምታደርግበት አግባብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ጠንካራና ገለልተኛ የሕግ አውጪ ተቋም ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ወሳኝ ሚና እንዳለውም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡- የአየርላንድ ኤምባሲ