Back

የፈረንሳይ ሕግ አውጪዎች ፌስቡክ እና ጉግል ላይ ቀረጥ እንዲጣል ወሰኑ

ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም

የፈረንሳይ ሕግ አውጪዎች የትራምፕ አስተዳደርን ዛቻ እና ማስጠንቀቂያ ወደጎን በመተው ፌስቡክ እና ጉግልን ጨምሮ በትላልቅ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ቀረጥ እንዲጣል ወሰኑ፡፡

ውሳኔው በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ፊርማ እንደሚፀድቅና ሕግ ሆኖ እንደሚፀና ይጠበቃል፡፡

ውሳኔው በፈረንሳይና በአሜሪካ መካከል ግጭት እንዳይቀሰቅስና ፈረንሳይን ሌላኛዋ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የንግድ ጦርነት ኢላማ እንዳያደርጋት ተሰግቷል፡፡

ምንጭ፡- ኒውዮርክ ታይምስ