Back

በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ላይ የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና የአቶ ታደሳ ካሳ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው

መጋቢት 2፣2011

በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ምዝበራ ላይ የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምኦንና  የአቶ ታደሳ ካሳ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው። 

እነ አቶ በረከት ስምኦን በዛሬው ችሎት ከጠበቃ ጋር ነው የቀረቡት፡፡ የተጠየቀው ተጨማሪ ቀን ተደጋጋሚ መሆኑ ተገቢነት የለውም ሲሉ ተቃውመዋል። 

ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው እንክብካቤ የራቁ በመሆናቸውና ካላቸው የጤና  ችግር አኳያ የዋስ መብቶቻቸው እንዲከበርላቸውም በጠበቆቻቸው በኩል  ጠይቀዋል፡፡

ይሁንእንጂ  ጥያቄዎቹ ከዚህ ቀደም በመጀመሪያው የችሎት ቀጠሮ ጊዜ የተከለከሉ በመሆኑ ጥያቄው በድጋሚ ሊነሳ አይገባም ሲል የምርመራ ቡድኑ ምላሽ ሰጥቷል።

ተጨማሪ ምርመራ የተጠየቀበት ምክንያት የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የኦዲት ምርመራ ላይ እየተወሰደ ያለው ጊዜ  ከስራ አኳያ እጅግ በጣም አጭር ነው መጨረስ አልተቻለም የሚል ምክንያት ቀርቧል፡፡

በተጨማሪም የጥረት  ኮርፖሬት የአክስዮን ሽያጭ ላይ  ሸያጩ ሲከናወን የነበሩ ግለሰቦች ቃለ መጠይቅ ለመስጠት ፍቃደኛ  ስለሆኑ እነሱን ለማካተት በሚል ነው የምርመራ ቡድኑ ተጨማሪ 14 ቀናትን የጠየቀው።

እነ አቶ በረከትም በተጠየቀው የተጨማሪ ቀናት መጨመር ለችሎቱ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የባህርዳርና የአካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም  በተጠየቀው የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ለነገ መጋቢት 3 ፣2011 8 ሰአት ላይ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሪፖርተር፡-  ራሄል ፍሬው