Back

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ

ጥር 03/2011

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ

 በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጠበቆች አስተዳደር እና የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለጹት የስራ ክፍሉ በዋናነት ትኩረት ሰጥቶ ከሚንቀሳቀስባቸው ተግባራት መካከል አንዱ የጠበቆችን ስነ-ምግባር መከታተልና ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ ውሳኔ ካገኙት 175 መዝገቦች መካከል 147 ጠበቆች ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

ከነዚህም መዝገቦች ውስጥ 5 በስነ ምግባር ችግር ጥፋተኛ ተብለው የታገዱ፣ 77 ፈቃድ በወቅቱ ባለማሳደስ በገንዝብ የተቀጡ፣ 54 ባለማሳደስ ለጊዜው የታገዱ፣ 7 በስነ ምግባር ችግር ጥፋተኛ ተብለው በገንዘብ የተቀጡ፣ 4 በማስጠንቀቂያ የታለፉ፣ 2 ክሱ አያስቀርብም የተባሉ እና 26 ደግሞ በነፃ የተሰናበቱ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ