Back

የብሪቲሽ አየር መንገድ የደንበኞችን ሚስጥራዊ መረጃ መጠበቅ ባለመቻሉ 183 ሚሊዮን ፓውንድ ተቀጣ

ሐምሌ 01፡ 2011 ዓ.ም

የብሪትሽ አየር መንገድ ባለፈው አመት ለወጣበት ምስጥራዊ መረጃ 183 ሚሊዮን ፓውንድ ቅጣት መክፈል ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡

ባለቤትነቱ “የኢንተርናሺናል ኤይር ላይን ግሩፕ’’ (IAG) የሆነው አየር መንገዱ በብሪታንያ የመረጃ ደህንነት ቢሮ (ICO)

በተላለፈበት ከፍተኛ የገንዝብ ቅጣት ተገርመናልም፣ ከፍቶናልም ብለዋል፡፡

የአየር መንገዱ ዌብሳይት ለኦንላየን መረጃ  ቀበኞች በመዘረፉ ነው ቅጣቱ የተጣለበት፡፡

የተያዙት መረጃዎች የ500 ሺህ ደንበኞች የይለፍ መረጃ፣ የክፊያ ካርድ፣ የጉዞ ዝርዝር፣ የሰዎች ስምና አድራሻዎች ይገኙበታል፡፡

አየር መንገዱ በወቅቱ ዌብሳይቱን ሃክ ስለመደረጉ ማስታወቁም ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ 28 የይግባኝ ቀናት አሉት ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ