Back

የ2019ኙ የኦስካር ሽልማት ያለ መደረክ መሪ እንደሚካሄድ ይካሄዳል

ታህሳስ 29፡ 2011 ዓ.ም

እ.እ.አ የ2019ኙ የኦስካር ሽልማት ለመጀመሪያ ግዜ ያለ መደረክ መሪ እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡

ድርጅቱ ከ3 አስርት ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ መድረክ መሪ የሽልማት ፕሮግራም የሚያካሄድበት ምክንያት የመድረክ መሪዉ አሜሪካዊዉ የፊልም ተዋናይ፤ ኮሜዲንና ኬቭን ሀርት በቲዉተር ገጹ በለቀቀዉ ጽሁፍ ተቋውሞው ስለገጠመው ነው፡፡

ይህንኑ ተከትሎ ተቋሙ ኬቭንን አግዶታል፡፡

የዘንድሮዉ የኦስካር ሽልማት ስነ ስርዓት ለየት ባለ መልኩ መድረክ መሪዎችን ተክተዉ የሚሰሩ  አዘጋጆች በመምረጥ  የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዘዉ እንዲቀርቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፣ ሃፊንግተን ፖስት