Back

45 ከመቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ያለው የዛምቢያ አየር መንገድ እንደገና ስራ ሊጀምር ነው

መጋቢት 26፣ 2011 ዓ.ም

የአገሪቱ ትራንስፖርት እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ብሬን ሙሺምባ አየር መንገዱ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ሶስተኛው ሩብ ዓመት ስራ ይጀምራል ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ የዛምቢያ መንግስት 55 ከመቶ ድርሻ ሲኖረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደሞ 45 ከመቶ ድርሻ በመያዝ በሽርክና ስራ ይጀምራል ተብሏል፡፡

ሚኒስትሩ አየር መንገዱ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአውሮፓ እና መካከለኛ ምስራቅ ሀገራት የመድረሻ መስመሮችን በተመለከተ ውይይት ማደረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 1ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎችን ያጓጉዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዛምቢያ አየር መንገድ ቀደም ሲል ኢትዮጵያዊውን ብሩክ እንደሻው ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙንሙ አስታውሷል፡፡
ምንጭ፡-ሉሳካ ታይምስ