ያለ ዕድሜ ጋብቻ አፍሪካን በየአመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር ያሳጣታል-አለም ባንክ

ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሴቶች ገቢና ምርታማነት በመቀነስ አፍሪካን በየአመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳጣ የአለም ባንክ ያወጣው ሪፖርት አመለከተ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ123 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የመሰረታዊ አገልግሎት ትራንፎርሜሽን መርሃ ግብር የ123 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፅድቋል፡፡

ታጥረው የቆዩ መሬቶች ላይ ያሉ ንብረቶችን የአ.አ ከተማ አስተዳደር ማንሳት ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ከባለሃብቶች በነጠቃቸውና ታጥረው የቆዩ ሁሉም አካባቢዎች ላይ ያለን አጥር እና ንብረት የማንሳት እርምጃ መውሰድ ጀመረ፡፡

የላሊበላ የቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ከ700 ሺህ ዶላር በላይ ወጪ ጥገና ተደርጎለት ተመረቀ

ከላሊበላ 11ዱ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት ውስጥ አንዱ የሆነው የቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ከአሜሪካ አምባሳደር ፈንድ እና ከአለም ሞኑመንት ፈንድ በተገኘ ከ700 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የጥገና ተደርጎለት ተመረቀ።

አዴፓ የክልሉን ህዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታወቀ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የክልሉን ህዝቦች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ደረጃ እንደሚሰራ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ።

የመውሊድ በዓል በብሄራዊ ደረጃ ተከበረ

የነብዩ ሙሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በብሄራዊ ደረጃ ተከበረ፡፡

የሶማሌ ክልል ም/ር መስተዳድር አቶ መስጠፋ ሙሐመድ ከሸበሌ ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

የሸበሌ ዞን ነዋሪዎች በሶማሌ ክልል ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የመፍትሄ አካል እንደሚሆኑ አስታወቁ፡፡

ኬንያ የባህር ጠረፍ ዘብ በማቋቋም ወደ ሥራ አስገባች

ኬንያ የባህር ዳርቻዎቿን የሚጠብቅ የባህር ጠረፍ ዘብን አቋቋመች፡፡

አልጀሪያ 93 ታዳጊዎችን ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች ማስለቀቋን አስታወቀች

ታዳጊዎቹ ለህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚውል ገንዘብ ሲለምኑ እንደነበር ተጠቁሟል።

በመንገዶች ላይ የሚገነቡ የፍጥነት መገደቢያዎች ወጥነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ጥናት ተጠናቋል

በመንገዶች ላይ የሚገነቡ የፍጥነት መገደቢያዎች ወጥነት እንዲኖራቸው የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ናይጄሪያ የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ናት - ዶ/ር ወርቅነህ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የናይጄሪያው አቻቸው ጄፍሪ ኦንያማ በተገኙበት የናይጄሪያ ዲፕሎማቶች የመኖሪያ ቤት ህንጻ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና ናይጀሪያ እ.ኤ.አ. ከ1960 ጀምሮ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከኒጀር ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን ወደፊት ለሚገነባው የአገሪቱ ኤምባሲ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኒጀር ፕሬዝዳንት አይሱፉ መሃመዱ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ለሚገነባው የኒጀር ኤምባሲ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር መከሩ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተወያይተዋል፡፡

መንግስት በታንዛኒያ በእስር የሚገኙ 224 ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ ጠየቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በዛሬው ዕለት ከታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኦገስቲን ማሂጋ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የአማራ እና የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ም/ቤቶች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

የአማራ እና የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ምክር ቤቶች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያና ኬንያ ለአካባቢው ትስስርና ሰላም በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ኬንያ ለአካባቢው ልማትና ትስስር በጋራ በመስራት ቀጠናውን ወደ ተሻለ ሁኔታ ለማሸጋገር የሚያደርጉትን ጥረት አሁንም አጠናከረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡

የኮዬ ፈጬ ቂሊንጦ ቱሉ ዲምቱ የውሀ ፕሮጀክት ተመረቀ

ለ440 ሺህ የከተማው ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጠው የኮዬ ፈጬ ቂሊንጦ ቱሉ ዲምቱ የውሀ ፕሮጀክትን ዛሬ ተመርቋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የመሬት ስሪት ማሻሻያ በፍጥነት ማጽደቅ አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

የደቡብ አፍሪካ መንግስት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የያዘውን የመሬት ስሪት ማሻሻያ በፍጥነት ማጽደቅ አስፈላጊ መሆኑን የሀገሪቱ ፓርላማ አስታወቀ፡፡