አርሰናልና ቼልሲ ለዮሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ

ትላንት ምሽት አርሰናል ወደ ጣሊያን ተጉዞ ናፖሊን በማሸነፍ ለዮሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ስልካቸው በችሎት በመጮሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

በችሎት የሚመላለሱ ተጠርጣሪዎችን አጅበው የመጡ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልካቸው በተደጋጋሚ በመጮሁ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት የፖሊስ አባላቱ ትጥቃቸውን ፈተው ዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ወታደራዊ ኃይሉ በሱዳን የሲቪል መንግስት እንዲኖር ይሠራል፡- የልዑካኑ መሪ

በሩሚ ሼክ አልጣይብ የተመራው የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ዛሬ ከኤ.ፍ.ድ.ሪ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ ጋር ከሂሩት ዘመነ ጋር በአዲስ አበበ ተወያይቷል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢቫንካ ትራምፕን አነጋገሩ

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የምትገኘውን የዋይት ሃውስ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

በከባድ የሙስናና ሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ሰሞኑን በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ ባስልጣናትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ለመገናኝ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ያሰጋኛል - ደቡብ ሱዳን

በሱዳን በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት አገሪቱን ለሶስት አስርት ዓመታት የመሯት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መወገድ የጎረቤት አገር ደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት እንዳያደናቅፈው አዲሲቱ አገር ሰግታለች፡፡

የፕሬዝዳንት አልበሽር ከስልጣን መልቀቅ አለመልቀቅ ሱዳንን ውጥረት ውስጥ ከቷታል

ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር የስልጣን መልቀቅ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ጦር መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

ለሰብአዊ መብት ዋና ኮሚሽነርነት የተመዘገቡ ዕጩዎች ተጣርተው በቀጣዩ ሳምንት ለምክር ቤቱ ይቀርባሉ

ለሰብአዊ መብት ዋና ኮሚሽነርነት የተመዘገቡ ዕጩዎችን አጣርቶ በቀጣዩ ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ እጩ አቅራቢ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡