የተከበሩ ሜትር አርቲስት የዓለም ሎረት አፈወርቅ ተክሌ የመታሰቢያ ሃውልት ተመረቀ

እጅግ የተከበሩ ሜትር አርቲስት የዓለም ሎረት አፈወርቅ ተክሌን የጥበብ ሥራዎችን በማደራጀት ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገለፀ፡፡

 

ባለስልጣኑ ከተባባሪ አካላት ጋር ያሠራው የአርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የመታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል፡፡

 

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ በምረቃው ሥነ ሥርአት ላይ እንደተገሩት ሐውልቱ የእርሳቸውን ሥራ እና ማንነት ለመዘከር ታስቦ የተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለሐወልቱ ግንባታ ከ15ዐ ሺህ ብር በላይ ውጪ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

 

በአሁኑ ወቅትም በአርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የተቋቋመውና በህይወት ዘመናቸው የሠሯቸውን የሥነ ጥበብ ውጤቶች በሙዚየም ደረጃ ለማደራጃት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡

 

በቀጣይም ጀምሩን በማጠናከር ለህዝብ ዕይታ ክፍት ለማድረግ ጥረቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ሪፖርተር፡- ይድነቃቸው ሰማው