የአሁኒቷ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍሬዎች

በሰለሞን አብርሃ

ትምህትና ጤና የአንድ አገር ማህበራዊ ለውጥ መነሻ አውታር ሆነው የሚያለግሉ ዘርፎች ናቸው፡፡ አገራት  የተማረና የሰለጠነ ዜጋ ከሌላቸው ፣ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ካልገነቡ ወደፊት የሚያደርጉት ሁለንተናዊ የለውጥና የእድገት ጉዞ አዳጋች ያደርገዋል፡፡

ለዚህም ሲባል ነው ጤናና ትምህርትን አገራት የመሰረታዊ መብት አንድ አካል አድርገው የሚመለከቱት፡፡

ኢትዮጵያም እንደ አገር  ባለፉት  25 ዓመታት በተከታታይ  ያስመዘገበችው የምጣኔ ሀብት እድገት የዚሁ ነፀብራቅ ውጤት መሆኑ አልቀረም፡ ፡ በተለይም ጤናው የተጠበቀ የሰው ሀብት ልማትን እውን ማድረግ መቻሉ ለተገኘው ሁለንተናው ለውጥ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ የኢፌዲሪ መንግስት ይሞግታል፡፡

የኢትዮጵያ የጤና ልማት

ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮች መካከል ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ መፍጠር ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ በጤናው መስክ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች ይህን ታሳቢ ያረጉ ነበሩ፡፡

የዛ 26 ዓመት ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በቀላሉ የሚታከምበት የጤና ማዕከልም እንዳሁኑ ወዲያው ማግኘት ቀላል ኘአልነበረም፡፡

ያኔ የነበረው የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታም በመድሀኒትም ሆነ በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ሃላ ቀር ከነበሩት ሀገሮች ተርታ የሚመደብ ነበር፡፡ የነበሩት የጤና ተቋማት ቁጥራቸው አንስተኛ ከመሆናቸው በዘለለ የተገነቡበት ቦታም በዋና ዋና ከተሞች እና የደርግን ወታደራዊ አስተላለፍ ታሳቢ ያደረጉ በመሆኑ አብዛኛውን የገጠሩን ህዝብ የዘነጉ ነበሩ፡፡ በዚህም ሳቢያ በጊዜው የነበሩት የጤና ተቋማት ተደራሽነት ፍትሀዊ አልነበረም ሊባል ይችላል፡፡

መከላከልን መርህ ያደረገው የኢትዮጵያ የጤና ፖለሲ

መንግስት የጤናውን ችግር ለማሻሻል በወሰደው እርምጃም በተለይ በ1986 በመከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ፖሊሲ በማውጣት በዘርፉ ለሌላው አለም ምሳሌ የሚሆን በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ከጤና ፖሊሲው የተቀዳውና በ1996 ዓ.ም የተቀረፀው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የማህበረሰቡን ጤና በማሻሻል ረገድ የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ በ16 የጤና ፓኬጆች ላይ ተመስርቶ እንዲተገበር የተደረገው ይህ ፕሮግራም ባለፉት ዓመታት በተለይም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ለተመዘገቡ የጤና ለውጦች ዓይነተኛ መሳሪያ ሆኗል፡፡ ፓኬጁንም ለማስፈፀም በአሁን ወቅት ከ39 ሺህ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ሰልጥነው በስራ ላይ መሰማራታቸው አገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እሰከማድረግ የደረሰ ስኬት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡

የጤና ተቋማት ግንባታን ስንመለከት ደግሞ በ1983 ዓ.ም 72 ብቻ የነበረው የመንግስት ሆስፒታሎች ቁጥር አሁን ከ411 በላይ ከፍ ብሏል፡፡ በተመሳሳይ 153 ጤና ጣቢያዎች ቁጥራቸው ወደ 3 ሺህ 562 አሻቅቧል፡፡ በዚህም ለ25 ሺህ ህዝብ አንድ የጤና ጣቢያ ለማዳረስ የተያዘውን ግብ ሙሉ በሙሉ ማሳካት የተቻለ ሲሆን የጤና ተቋማቱን አገልግሎት የማሻሻልና ግብአቶችን የማሟላት ሥራም ትኩረት ተሰጥቶት ተሰርቷል፡፡ የጤና ኬላዎችም አሁን ላይ ብዛታቸው ከ16 ሺህ 447 በላይ ደርሰዋል፡፡

ሆኖም የጤና ተቋማትን በስፋት በመገንባት የጤና አገልግሎት ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የተቻለ ቢሆንም በየደረጃዉ ህዝቡን ያረካና ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ከማቅረብ አንፃር ገና ብዙ መስራትን እንደሚጠይቅ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል፡፡

በመንግስትና መንግስታዊ ባለሆኑ አካላት በተከናወኑ ተግባራት ከ26 ዓመት በፊት 38 በመቶ ብቻ የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አግልግሎት ሽፋን በአሁን ወቅት መቶ በመቶ  ማዳረስ ተችሏል፡፡

ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የፈራው የሰው ኃይል

በጤናው ዘርፍ በተከናወነው የሰዉ ሀይል ልማት በአሁን ወቅት በአጠቃላይ ከ160 ሺህ በላይ የጤና ባለሞያዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህም በ1983 ዓ.ም ከ40 ሺህ ከማይበልጠው አጠቃላይ የጤና ባለሞያዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር የጤና ባለሞያዎችን ቁጥር ለመጨመር ከፍተኛ ስራ መሰራቱንና እመርታዊ ለውጥ መመዝገቡን ያሳያል፡፡

አሁን ላይ ከ46 ሺህ በላይ ነርሶች፣ ከ6 ሺህ በላይ የጤና መኮንኖች፣ ከ8 ሺህ 500 በላይ አዋላጅ ነርሶች፣ ከ5 ሺህ 540 በላይ ሀኪሞች በመንግስት የጤና ተቋማት ውስጥ በመስራት ላይ ናቸው፡፡

በጤና ተገልጋዩ ማህበረሰብ ዘንድ የተገኙ ውጤቶችና ችግሮች

ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በመንግስት፣ በህብረተሰብና ባለድርሻ አካላት በተከናወኑ ተግባራት የህብረተሰቡን ጤና በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል ተችሏል፡፡ ለአብነትም በእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ የተመዘገው ውጤት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የምዕተ ዓመቱን ግብ ከተቀመጠው ጊዜ በ3 ዓመት ቀድማ ማሳካቷን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተረጋግጧል፡፡  በወሊድ ወቅት የሚያጋጥሙ የእናቶች ሞትን አሁን ላይ ከ79 በመቶ በላይ መቀነስ እንደተቻለም ነው የሚነገረው፡፡   

ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራም በእዚህ ረገድ የተገኘው ውጤት አንስተኛ በመሆኑ በቀጣይ ቀሪ ስራ እንደሚጠይቅ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ ከህፃናት ሞት ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው የጨቅላ ህፃናት ሞት ነው፡፡ የእዚህ አንዱ ምክንያት ደግሞ አብዛኛው እናቶች የሚወለዱት ተገቢ እንክብካቤ በማያገኙበት በቤት ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡

ከተላላፊ በሽታ አንፃርም በሀገሪቱ በኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ በወባና በቲቢ በሽታ የሚከሰተው የሞት መጠን በእጅጉ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ በኤች አይ ቪ ቫይረስ አዲስ የመያዝ መጠን ከ10 ዓመት በፊት ከነበረዉ ጋር ሲነፃፀር በ90 በመቶ ቀንሷል፡፡ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተሰራዉ ጠንካራ ሥራ ባለፈ 10 አመት በሽታዉ በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰት ማድረግ ሲቻል በበሽታው የሚከሰትው የሞት መጠን ከ60 በመቶ በላይ ቀንሷል፡፡ ህፃናትን የሚያጠቃው ‹‹የልጅነት ልምሻ›› ወይም የፖሊዮ ቫይረስ በሀገሪቱ እንዲጠፋ ማድረግ ተችሏል፡፡ እነዚህ ተላላፊ በሽታዎች ስርጭታቸው በአመዛኙ በቁጥጥር ስር ቢውሉም የአካባቢና የግል ንጽህና ባለመጠበቅ እንዲሁም በድርቅ አደጋ ሳቢያ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውንና የሰው ህይወትን የሚቀጥፈው የአተት/አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት/ በሽታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ርብርብ ሊደረግ ይገባል፡፡  

ከዚህም ባሻገር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጤናው ዘርፍ በመልካም አስተዳደር በተለይም በአገልግሎት አሰጣት ለውጦች ቢኖሩም አሁንም ይብዛም ይነስም እዚህም እዛም የሚታዮና በተገልጋይ ህብረተሰቡ ቅሬታ የሚያስነሱ ጉዳዮች ያሉ በመሆናቸው በወቅቱ ፈጣን ምላሽ ሊያገኙ ይገባል፡፡

እንግዲህ በአጠቃላይ በጤና ዘርፍ የተገኙ ለውጦች የዜጎችን በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ ጨምረውታል፡፡ በ1980ዎቹ መጀመሪያ የነበረው የ45 ዓመት የእድሜ ጣሪያ ዛሬ ላይ ወደ 65 ዓመት ከፍ ብሏል፡፡

በሀገሪቱ እየተመዘገበ ካለዉ ፈጣን እድገት ጋር በተያያዘ የከተሞች መስፋፋትና  የህዝቡ የአኗኗር ዘይቤም በዚያዉ ልክ እየተቀየረ መጥቷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ቅድሚያ ትኩረት ያላገኙ እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና ካንሰር የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሁን በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ እየተለወጠ የመጣዉን የበሽታዎች ሁኔታ ታሳቢ ያደረገና ከልማት እንቅስቃሴ ጋር የሚተሳሰር የጤና አገልግሎት በቀጣይ ለመዘርጋት የጤና ፖሊሲውን መከለስ እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡

ጤናን ስናስብ ውሃን አንዘነጋም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ባለፉት 26 ዓመታት በገጠርና በከተማ የውሃ አቅርቦት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም አሁንም በዘርፉ ያለው ፍላጎትና አቅርቦት ባለመጣጣሙ በህዝቡ ዘንድ በየጊዜው እሮሮና ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል፡፡ ችግሩንም ለመቅረፍ መንግስት እየሰራው ነው ቢልም ጥረቱ ፍጥነት ካልታከለበት የሚያስከትለው መዘዝ መገመት ስለማያዳግት መፍትሄው በወቅቱ ሊበጅ ይገባል፡፡

ኢትዮጵያ ከትምህርት ዘርፍ ልማት አንፃር

በየትኛውም አለም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ከሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የሰው ሀይል ልማት ወሳኝ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህም መስክ የሰለጠነ አምራች ዜጋ የሚያፈራው የትምህርት ዘርፉ ተጠቃሽ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ባለፈው ሩብ ምዕተ አመት ውስጥ በተለይም በሽግግር ዘመኑ የመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት ሽፋን 19 በመቶ ያህል ብቻ ነበር፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዮት ደግሞ የትምህርት ስራው የነበረበት ችግር አገልግሎቱ በሚገባ አለመስፋፋቱ ብቻ ሳይሆን በውስን ደረጃ እየተሰጠ ያለው ትምህርትም ቢሆን ፍትሃዊ አለመሆኑ ጭምር ነው፡፡ በገጠርና በከተማ፣ በክልልና በክልል፣ በወንድና ሴት መካከል ያለው የትምህርት አገልግሎት ስርጭት እጅግ ያልተመጣጠነ ነበር፡፡

ባለፉት ዓመታት በተከናወነው ተግባር ይህንን እውነት ከመሰረቱ ለመቀየርና ሀገሪቱን በትምህርት ዘርፍ በምሳሌነት የምትጠቀስ ለማድረግ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በተለይ በ1986 የወጣውን የትምህርት ፖሊሲ ተከትሎ የሀገሪቱ ትምህርት ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት የሚበጁ ዜጎችን የሚያፈራና የፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሳሪያ እንዲሆን ያስቻሉ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

የትምህርት መስፋፋትና ተደራሽነት  

በቅድሚያ የተሰራውም ትምህርትን ማስፋፋትና ፍትዓዊ የማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን ቁጥር የማሳደግ ስራዎች ናቸው፡፡  ትምህርት ሚኒስቴር እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀረው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በአሁኑ ጊዜ 32 ሺህ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ 2 ሺህ ገደማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ 901 የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጆችና ፣  35 ዩኒቨርስቲዎች በመክፈት አሁን የተገኘውን የትምህርት ዘርፉን ስኬታማ ቅብብሎሽ እውን ለማድረግ አስችሏል፡፡

በዘርፉ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የታየው የተሳትፎ ለውጥ በአብነት የሚጠቀስ ነው፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች በትምህርት ገበታ ተገኝተው እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደተናገሩት ለትምህርት ዘርፉ በተሰጠው ልዮ ትኩረት በዘርፉ ልማት ስር ነቀል ለውጥ ተመዝግቧል፡፡ አሁን በአሁኑ ወቅት ከአጠቃላይ የኢትዮያ ህዝብ  ¼ው  ወይም እስከ 27 ሚሊዮን የሚጠጋው ዜጋ  ትምህርት ቤት ውስጥ መገኘቱ ለትምህርት የተሰጠው ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት እንደምታው

ባለፉት 26 ዓመታት በትምህርት ተደራሽነትን፣ ተሳትፎና በመሰል ስራዎች ለሌሎች ሀገሮች አርዓያ የሚሆኑ ተግባራት ቢፈፀሙም በተለይ በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ጉዳይ ላይ ግን አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም አውጥቼ በትኩረት እየሰራው ነው ሲል ይናገራል፡፡

የትምህርት ጥራት አንዱ መለኪያ በውጤቱ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በተለይ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በየዓመቱ የሚመረቁ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በየጊዜው ቁጥራቸው እጨመረ ይገኛል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎቹም በሰለጠኑበት መስክ በሀገሪቱ የሚያገኙት የስራ እድል ያን ያህል አመርቂ የሚባል አይደለም፡፡ የትምህርት ዘርፉን ስኬት የሚገዳደረው ይህን ችግር በጊዜ እልባት ካላገኘ ደግሞ ውሎ አድሮ በሀገሪቱ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ ምንጭ መሆኑ አይቀርም፡፡ ችግሩንም ለመቅረፍ መንግስት በተለያዮ ጊዜዎች ወጣቱ ስራ ጠባቂ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ እንዲሆን እንዲሁም በጥቃቅንና አንስተኛ ዘርፎች ተሰማርተው እንዲሰሩ ጥሪውን እያቀረበ ይገኛል፡፡ በቅርቡ በመላ አገሪቱ በተካሄደ የስራ አጥነት ምዘገባ እንኳን 5 ሚሊዮን ስራ አጥ ወጣቶች መለየታቸውን መንግስት ገልጿል፡፡ የትምህርቱ ዘርፍ ያመጣውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ስራ ፈጣሪ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ዳር ሊያደርስ የሚችል አሰራር መዘርጋትን ይጠይቃል፡፡

ለነገዋ ኢትዮጵያ …

በአጠቃይ ባለፉት 26 አመታት ኢትዮጵያ የትምርትና ጤና ዘርፉን ከሚመደበው አገራዊ በጀት ትልቁን ድርሻ እንዲይዝ በማድረግ በርካታ ተቋማትን ስትገነባ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ ጤናማና የተማረ ማህበረሰብ አገር የመቀየርና የማሳደግ ትልቅ ተልዕኮ እንዳለው በመገንዘብ የተገኘ የልፋት ፍሬ ነው፡፡

በዚህም ባለሁለት አሀዝ እያደገ ያለ ፈጣን ምጣኔ ሀብት መገንባት አስችሏል፡፡ይህም የመጨረሻ ግቡ ወደ መካከለኛ ገቢ ከተሸጋጋሩ አገራት ኢትዮጵያን ማቀላቀል ነው፡፡

ይህ የሚሆነው ደግሞ እሁን ያለው የጤናና የትምህርት ልማት ተደራሽነት ጥራት ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ ነው  የዘርፉ ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡ ትላንት ላይ  ከምንም ተነስቶ ዛሬ  ላይ የተገኙት የዘርፉ ውጤቶች ጥራት ከታከለባቸው ስራ ፈጣሪ ጠንካራ ዜጋ በማፍራት ዘለቄታዊ የሆነ ማህበረሰባዊ ለውጡን ማፋጠን ያስችላልም ባይ ናቸው፡፡

1983 ግንቦት ሀያ የቀደደው ጎህ ወደ አዲስ ምዕራፍ በስኬት እንዲሸጋገር ካስፈለገ በጤናማና በተማረ ዜጋ የተጀመረው ጥረት ጎልበቶ በምርምርና በሌሎችም ዘርፎች አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ከፍ ብላ የተቀመጠች ኢትዮጵያን መፍጠር የመንግስትና ባለድርሻዎች የመሪነት ሚና ሆኖ ይቀጥላል፡፡  

 

አባሪ ሰንጠረዥ

   የኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና እድገት በ2007 ዓ.ም.

 1. የት/ቤቶች (የተቋማት) ብዛት በየደረጃው

ተ.ቁ

ተቋማት

1983 ዓ.ም.

1993 ዓ.ም.

2007 ዓ.ም.

 1.  

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት (1-8)

8,434

11,780

32,048

 1.  

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (9-12)

275

424

2,333

 1.  

የቴ/ሙ/ት/ሥ (የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ) 

17

23

901

4.

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

3 እንስትቲዩት፣ 5 ኮሌጆችና 2 ዩኒቨርሲቲዎች

1 እንስትቲዩት፣ 3 ኮሌጆችና 6 ዩኒቨርሲቲዎች

1 ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና 35 ዩኒቨርሲቲዎች 

 

 

5.

የግል (መንግስታዊ ያልሆኑ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

 

---

6

98

 

 1. የተማሪዎች ብዛት

ተ.ቁ

ተቋማት

1983 ዓ.ም

ድምር

1993 ዓ.ም

ድምር

2007 ዓ.ም

ድምር

ወንድ

ሴት

ወንድ

ሴት

ወንድ

ሴት

 1.  

አንደኛ ደረጃ(1-8)

1,200,93

862,242

2,063,635

4,416,189

2,985,284

7,401,473

10,237,169

9,129,085

19,366,254

 1.  

ሁለተኛ ደረጃ (9-12)

231,115

184,967

416,082

430682

305492

736174

1,145,224

1,015,074

2,160,298

 1.  

የቴ/ሙ/ት/ሥ (የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ)

2,120

469

2,509

3,782

779

4,561

167,881

184,263

352,144

 1.  

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ፕሮግራሞች   አጠቃላይ   ተማሪዎች ተሳትፎ 

15,942

1,953

17,895

58,780

13,450

72,230

426,297

215,251

641,548

 1.  

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች

አጠቃላይ   ተሳትፎ

15,942

1,953

17,895

29,544

5,993

35,637

245,872

129,544

375,416

 1.  

የግል (መንግስታዊ ያልሆኑ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመደበኛና መደበኛ ያልሆኑ ፕሮግራም ተማሪዎች  አጠቃላይ   ተሳትፎ 

 

---

--

---

7,477

3,698

11,175

63,556

50,140

113,696

 

3. የመምህራን ብዛት

ተ.ቁ

ተቋማት

1983 ዓ.ም

ድምር

1993 ዓ.ም

ድምር

2007 ዓ.ም

ድምር

ወንድ

ሴት

ወንድ

ሴት

ወንድ

ሴት

 1.  

አንደኛ ደረጃ (1-8)

51,360

17,087

68,457

84,402

36,675

121,077

230,413

137,576

367,989

 1.  

ሁለተኛ ደረጃ (9-12)

10,811

1,057

11,868

12883

1146

14029

59,625

11,362

70,987

 1.  

የቴ/ሙ/ት/ሥ

---

----

338

456

45

501

16,912

4,918

21,830

 1.  

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

1,566

121

1,687

2,730

227

2,957

22,499

2,591

25,090

 1.  

የግል (መንግስታዊ ያልሆኑ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

 

---

---

---

256

19

275

2,173

489

2,662

 

 

 

 

ዋቢ መረጃዎች

1.ትምህርት ሚኒስቴር

2.ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር