ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ባሉት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ተፈላጊውን የትምህርትና የሥራ ልምድ መስፈርት የሚያሟሉትን አመልካቾች ተቀብሎ በማወዳደር በኮንትራትና ፍሪላንሰርነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ለተገለጹት ክፍት የሥራ መደቦች ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በኮርፖሬሽኑ የሰው ኃይል ምልመላና መረጣ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1020 በመቅረብ ወይም ተወካይ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ፡፡