የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር በአዲስ አበባ በይፋ ተቋቋመ

ሰኔ1፤2009

የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር በኢፌድሪ የበጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበራት ኤጄንሲ እውቅና በማግኘት በአዲስ አበባ በይፋ መመስረቱን አስታውቋል፡፡

ማህበሩ በመላው አገሪቱ ከ2 ሺህ በላይ ዲጄዎችን በአባልነት በመመዝገብ የዲጄ ሞያ አገልግሎትን በተቀናጀ መንገድ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ አላማ አድርጎ መመስረቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዲጄ አሮን ከበደ አስታውቋል፡፡ በአገራችን በልምድ እየተሰራ ያለውን የዲጂ ሞያ በትምህርት ለመደገፍም ማህበሩ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የዲጄ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም የሚያስችል ጥናት በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስታወቀው፡፡

የማህበሩ መቋቋም በመላው አለም የሚገኙ ፕሮፌሽናል ዲጄዎችና ፕሮዲውሰሮች ጋር በመተባበርም ለአባላቱ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ ማህበሩ በአገሪቱ ውስጥ ለዲጄ ሞያ ያለውን የተዛባና ዝቅተኛ አመለካከትም ለማሻሻል እንደሚሰራና ለአባላቱ የሞያ መብት ዘብ እንደሚቆም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡

በናትናኤል ፀጋዬ