የአፍሪካዊያን ሞኖፖሊ - ኢቦላየአፍሪካዊያን ሞኖፖሊ - ኢቦላ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በጌቱ ላቀው

አርታኢ፡- ሰዒድ አለሙ

የአፍሪካዊያን ሞኖፖሊ - ኢቦላ

የያዝነው 2006 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ማለትም ባለፈው መጋቢት  በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ በዋናነት ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ናይጄሪያ እና ጊኒን ቀዳሚ ተጠቃሽ ሀገራት አድርጓቸዋል። ከዚህ ቀደም የኢቦላ ቫይረስ በተደጋጋሚ ሲጎበኛት የነበረችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም ቫይረሱ ወደሐገሯ መግባቱን በሳምንቱ መጨረሻ አስታውቃለች። በእነዚህ ሀገራት እየተስፋፋ የመጣው ይህ በሽታ እዚያው የሚቀር ብቻ ሣይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ስጋቱ አንዣቦባቸዋል። በአጭር ጊዜ ብቻ ከአራት ሀገራት ከ1 ሺህ 4 መቶ በላይ አፍሪካውያን ወደ ግብዓተ መሬት እስገብቶ ከ2ሺ 6 መቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የቫረሱ ወረርሽኝ አዳርሷቸዋል፡፡

የኢቦላ ቅድመ ታሪክ

አፍሪካ በታሪኳ የበርካታ በሽታዎች መነሻም መድረሻም በመሆን የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂ እየሆነች አልፋለች። አሁንም ምዕራብ አፍሪካን እያመሰ ያለው ኢቦላ የተባለው በሽታ አፍሪካን እንደ ፋሽን አንዱን ችግር ስትሻገር ብቅ ያለው ሌላኛው ጋሬጣ ሆኖ ብቅ ብሎባታል።

አሁን በምእራብ አፍሪካ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው የኢቦላ ቫይረስ ለአፍሪካ የመጀመሪያ ወይም አዲስ የሚባል በሽታ አይደለም።  ምክንያቱም አሁን ተነሳ የተባለው የኢቦላ በሽታ በአፍሪካ ታሪክ ለ24ተኛ ጊዜ በመሆኑ ነው። እንደ አሁኑ ባይከፋም ላለፉት 38 አመታት የሰውን ልጅ እና እንስሳት ለሞት ሲዳርግ የነበረ በሽታ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢቦላ ቫይረስ በጎርጎሮሳውያኑ 1976 በሱዳን "ነዛራ" እንዲሁም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ "ያምቡክ" በሚባሉ አካባቢዎች ተነስቶ እንደነበር የሚጠቁም መረጃ ይገኛል። ቫይረሱ ታድያ ኮንጎ ውስጥ ኢቦላ በተባለ ወንዝ አቅራቢያ በመገኘቱ  ኢቦላ የሚለውን  ሥያሜ በወቅቱ አግኝቷል።


Pages: 1  2  3  4  5  6  7  8  9