ክፍት የስራ ማስታወቂያ

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

  

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከ TVN Group ጋር በመሆን በጣሊያን ኤምባሲ ትብብር የጣሊያን ሴሪ አ የ2015/16 ጨዋታዎችን በ EBC3 በቀጥታ ለማስተላለፍ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ፕሮግራሙን የሚያስተባብር ሙያተኛ በኮንትራት ቀጥሮ ለማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በኮርፖሬሽናችን 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1020 ዋናውንና ኮፒ መረጃ በማቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 1. የስራ መደብ መጠሪያ፡- አስተባባሪ
 2. ብዛት ፡- አንድ
 3. ፆታ፡-ሴት
 4. ዕድሜ ፡-ከ18- 25
 5. እንግሊዘኛና አማርኛ ቋንቋ አቀላጥፎ መናገር የምትችል
 6. በማንኛውንም የትምህርት መስክ የኮሌጅ ዲፕሎማና ከዚያ በላይ ያላት
 7. በዘርፉ በማስተባበር የተገኘ የስራ ልምድ ይመረጣል
 8. ዋና ተግባራት፡-ለቀጥታ ስርጭት የሚጋበዙ እንግዶች ማስተባበር፣ መለየት፣    ለፕሮጀክቱ የሚመደበውን ሀብት መከታተል በአጠቃላይ የፕሮጀክቱን መረጃዎች አደራጅቶ መያዝና ከዚሁ ተዛማጅ ተጨማሪ ተግባራት ናቸው
 9. የስራ ቦታ፡ በኢብኮ እና አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ
 10. ደሞዝ፡-በወር ብር 4000፡00 /አራት ሺህ ብር/ ጥቅል ደሞዝ
 11. የኮንትራት ጊዜ፡- ቅጥሩ ከሚፈፀምበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ9 ወራት ሆኖ   የፕሮጀክቱ ውጤታማነት እየታየ እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ ሊራዘም ይችላል፡፡

 

    የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን