ቻይናዊው ደረጃዎችን በጭንቅላቱ በመውጣት የአለም ክብረወሰን ሰበረ

ቻይናዊው በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ "Guinness World Book of Records" በጭንቅላቱ ቆሞ ደረጃዎችን በመወጣት ክብረወሰኑን ሰብሯል።

ቻይናዊው ሊ ሎንግሎንግ የተባለው ግለሰብ በዚህ ሳምንት 36 ተከታታይ ደረጃዎችን በራሱ ቆሞ በመውጣት ተመልካቹን አስደንቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ክብረወሰኑን ለመስበር ሞክሮ ያልተሳካለት ሊ ሎንግሎንግ ጠንካራ ልምምድ ባማድረግ ስሙን ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችሏል፡፡

ክብረወሰን ለማግኝት ጥብቅ መመሪያዎች መከተል አስፈላጊ መሆኑ የተለጸ ሲሆን ተወዳዳሪው ከአምስት ሰከንዶች በላይ መቆም እንደማይችል እንዲሁም ሌላ የሰውነት ክፍሉ ደረጃውን መንካት እንደማይችል ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፤ ጊነስ ዎርልድ ኦፍ ሪከርድስ