የውድድር ምዝገባ ጥሪ

1.የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና እና ፕሮግራሞች ቻናሉ አዲስ ከሚያቀርባቸው ዝግጅቶች መካከል የንግድ ሥራ ተሰጥኦ ውድድር አንዱ ነው፡፡ ውድድሩ የንግድ ሃሳብን በማውጣት ችግር ፈቺ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር የሚያሸልም ይሆናል፡፡

2. ተወዳዳሪዎች በአካባቢያችሁ፣ በክልላችሁ እንዲሁም በሀገር ደረጃ ያሉ የልማት ችግሮችን ይፈታሉ የምትሏቸውን መነሻ የፕሮጀክት ሃሳብ በማቅረብ መወዳደር ትችላላችሁ

3.ውድድሩ ፆታን የትምህርት ደረጃን የማይገድብ ሲሆን እድሜ ግን ቢያንስ ፕሮጀክቲን ወደ ተግባር ለማዋል በሚያስችል እድሜ ላይ ያለ ቢሆን ይመረጣል

4. ለውድድር የሚቀርቡ ተሳታፊዎች ማሟላት ያለባቸው የውድድሩ ፕሮፖዛል ከ5 ገጽ መብለጥ የለበትም

4.1 የመጀመሪያው ገጽ የተወዳዳሪው ስም፣ የትምህርት ደረጃ፣ እድሜ፣ ፆታ፣ የተወዳደሩበት ክልል ይህ በመጀመሪያው ገጽ ላይ የሚጻፍ ይሆናል

4.2 ከገጽ 2-5 ባሉት ስለ ፕሮጀክቱ የሚገልፅበት ይሆናል

4.3 የንግድ ሃሳቡ ዋና ጭብጥ

4.4 የንግድ ሃሳቡ ፈጠራ ነክ መሆኑ

4.5 በገበያ ተፈላጊነትና ተወዳዳሪ መሆኑ

4.6 የኢንቨስትመንት ወጭው ተአማኝነቱ /የተወዳዳሪው ድርሻም ይገለፃል/

4.7 ፕሮጀክቱ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ተስማሚነት

4.8 የምርቱ ዘላቂነትና ትርፋማነት፣ አዋጭነቱ

4.9 የተወዳዳሪው የአመራር ብቃትና ክህሎቱ

4.10ተወዳዳሪዎች በግል፣ በቡድን፣ ወይም በማህበር መቅረብ ይችላሉ

4.11ተወዳዳሪዎች 3*4 የሆነ ማንነታቸውን የሚገልፅ አንድ ፎቶግራፍ አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል

4.12 በቡድንና በማህበር ለሚወዳደሩ የቡድን ሰብሳቢና የማህበሩ ሰብሳቢ ፎቶ ከፕሮጀክቱ ጋር ይያያዛል

4.13 የፕሮጀክት ጽሁፍና ውድድሩ በአማርኛ ይሆናል

4.14 አንድ ተወዳዳሪ ከአንድ በላይ በሆኑ ፕሮጀክቶች መወዳደር አይችልም

4.15 የምዝገባ ቦታ በሁሉም ክልሎች ባሉ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ማሰራጫ ጣቢያዎች ጽ/ቤቶች ወይም ፖስታ ሳጥን ቁጥር 5544 ወይም 1020 በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ

4.16አዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ተወዳዳሪዎች በፖ.ሣ.ቁ 5544 ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1020 በመላክ እና በአካል በኮርፖሬሽኑ መረጃ ክፍል ሰነድ በመስጠት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

5. እንዲሁም በኢቢሲ ዌብሳይት www.ebc.et ተጨማሪ መረጃ ታገኛላችሁ

6.በተጨማሪም በፌስቡክ Ethiopian Vroadcasting Corporation @ebc 1 news መረጃ ማግኘት ይቻላል

7. እንደዚሁም Business.talent@ebc.et ወይም ebcbusinesstalent@gmail.com ዶክመንት መላክና መመዝገብ ትችላላችሁ

8. ተወዳዳሪዎች ኢትዮጵያዊ መሆን አለባቸው

የምዝገባ ጊዜ ከሚያስያ 01 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም ይሆናል

የምዝገባ ጊዜ ማጠናቀቂያ ሚያዝያ 15 ቀን የነበረው እስከ ሚያዝያ 22 ቀን ተራዝሟል::

ዘግይቶ የመጣ አመልካችን አናፋተናግድም