ቻይና በመጪዎቹ አራት አመታት የፈጣን ባቡር ሽፋኗን ወደ 3ዐ ሺ ኪሎ ሜትር ልታሳድግ ነው

ታህሳስ 20 ፣2009

ቻይና በመጪዎቹ አራት አመታት የፈጣን ባቡር ሽፋኗን ወደ 3ዐ ሺ ኪሎ ሜትር ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን አስታወቀች፡፡

ሀገሪቱ እየገነባች ያለችው የባቡር መስመር እና የግዙፍ ድልድይ ግንባታ የግዛቶቿን የንግድ ትስስር የበለጠ ለማሳደግና የተቀናጀ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑን የአገሪቱ መንግስታዊ ልሳን የሆነውን ዘ ኃይት ፔፐር ጠቅሶ ሽንዋ ዘግቧል፡፡

ቻይና በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ለመዘርጋት ላሰበችው የባቡር መስመር ግንባታ ግማሽ ትርሊዮን ዶላር ገደማ በጀት ይዛለች ተብሏል፡፡

የሚዘረጋው  ዘመናዊ የባቡር  መስመር በፍጥነት እያደገ ከመጣው የቻይና የህዝብ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እና የዋና ዋና ከተሞችን ትስስር 80 በመቶ ለማድረስ የሚያስችል እቅድ መሆኑንም መንግስት ገልጿል፡፡