በአፍሪካ የተከሰተው ፀረ ሰብል ነፍሳት በአህጉሪቱ ገበሬዎች ህይወት ስጋት መደቀኑን ተመራማሪዎች አስታወቁ

ጥር 29፣ 2009

በአፍሪካ የተከሰተው ፀረ ሰብል ነፍሳት መንጋ በአህጉሪቱ  ገበሬዎች ህይወት ስጋት መደቀኑን  ተመራማሪዎች አስታወቁ።


ተመራማሪዎች በአፍሪካ አገራት የበቆሎ  ሰብልን ክፉኛ  እያወደመ  ያለው ተባይ(armyworm) በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ  አፋጣን እርምጃ  እንዲወሰድ ጠይቀዋል።

አለም አቀፉ የግብርናና ስነ ህይወታዊ  ሳይንስ የተሰኘው ተቋም እንዳለውየተከሰተው ፀረ ሰብል ተባዩ በበቆሎ  ላይ እያደረሰ ባለው ጉዳት አጉሪቱን በመግብ ዋስትናና በግብርና ንግድ ላይ ኪሳራ ሊያደርስባት እንደሚችል ከወዲሁ አስጠንቅቋል።

የፀረ ሰብል ተባዩ መንጋ ከአፍሪካ አልፎ ወደ ኢሲያ እንዳይሸጋገርም ስጋት ደቅኗል።

እንደ ቢቢሲ  ዘገባ የአለም ምግብና እርሻ ድርጅት ፋኦ በጉዳዩ  አሳሳቢነት ላይና ስለሚወሰደው አፀፋዊ ምላሽ በቀጣዩ ሳምንት  ለመምከር በዝምባቡው ቀን ቆርጧል ብሏል።

በቆሎን እያጠቃው ያለው ይህ ፀረ ሰብል ተባይ መንጋ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሙሉ  ሰብሉን የሚያወድም ነው ተብሏል። በአፍሪካ ሲታይ የመጀመሪያው መሆኑንምም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

እንደ  ቢቢሲ ዘገባ ዛምቢያ ይህንን ፀረ ቦቆሎ ተባይ የሚያደርሰውን ጉዳት  ለመከላለክ በሄሊኮፕተር ፀረ  ተባይ መደሃኒት  በመርጨት ላይ ትገኛለች።