የሳህል ቀጠና አገራት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚያስችል የጋራ ግብረ ኃይል ሊመሰርቱ ነው

የካቲት 01 ፣2009

የሳህል ቀጠና አገራት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚያስችል የጋራ ግብረ  ኃይል ሊመሰርቱ  ነው።

የሰሃል በረሃ የሚያገናኛቸው አምስት አገራት ናቸው የጋራ የፀረ  ሽብር ኃይሉን ለመመስረት የተስማሙት።

በጉዳዩ  ላይ  የማሊ ፣ኒጀር፣ ሞሪታኒያ፣ ቡርኪናፋሶና ቻድ ፕሬዝዳንቶች ከስምምነት መድረሳቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

አገራቱ  አዲስ የሚመሰርቱት የጋራ የፀረ ሽብር ኃይል እውን ለመሆንና  የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ከአፍሪካ ህብረትና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይሁንታ እንደሚጠብቁ አገራቱ  ትላንት ይፋ ባደረጉት መግለጫ  አመልክተዋል።

አገራቱ   እንደ ቦኮ  ሀራምና ከአልቃኢዳ  ጋር ግንኙነት አላቸው በሚባሉ ቡድኖች ላይ መጠነ  ሰፊ  ዘመቻ በማድረግ የሽብር ቡድኖቹን ስጋት መቀንስ ዋንኛ አላማቸው መሆኑን የአሶሼትድ ዘገባ አመልክቷል።